=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=
ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ
1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።
2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።
3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።
4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
![]() =<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=
![]() በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው። ![]() |
---|
ፍጥረታት በሙሉ ከጥንት ጀምሮ፤
መላዕክቶች ሳይቀሩ ኢብሊስን ጨምሮ፤
የሰው ልጅ ሲፈጠር ከአዳም ጀምሮ፤
እንዲኖር ነበር ትዕዛዙን አክብሮ፤
የአሏህን ሃያልነት ባንድነት መስክሮ፤
አሏህ አልፈጠረም አንዳች ነገር፤
እንዲኖር እንጂ በሱ ትዕዛዝ ስር፤
ከፍጥረታት በሙሉ፤
ከአድማስ እስከ አድማስ ያሉ፤
እፅዋት አራዊቶች ዛፍና ቅጠሉ፤
አላማ አላቸው የመፈጠራቸው፤
የአሏህን አንድነት መስካሪዎች ናቸው፤
የተፈጠረበትን አላማ ዘንግቶ፤
የአሏህን ራህመት ቀና መንገድ ትቶ፤
ነፍሱን ተከተለ እሮጠ ነጎደ፤
በጥፋት ጎዳና ራሱን አዋረደ፤
እሩጦ መጨረሻውን ሲያጣ፤
የአሏህን ትዕዛዝ በቅጡ ሳይወጣ፤
ጭንቀት ሲፈጥርበት የምድር አለሙ፤
አልገባኝም ይላል የኑሮ ትርጉሙ፤
እራሱን ያጠፋል እስከ ዘላለሙ፤
እውነትም ያልገባው የዚች አለም ኑሮ፤
ሁልጊዜ ይኖራል በጭንቀቱ ታስሮ፤
የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ |
---|